La Gare Amharic Logo

ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ግዙፍ እና ዘርፈ-ብዙ የመኖሪያ ግንባታዎች አንዱ የሆነው ላጋሬ፣ በአዲስ አበባ የመጀመሪያውን ቅንጡ የመኖርያ ህንፃ ለሽያጭ በማቅረብ ታላቁን እርምጃ በተግባር ጀመረ፡፡ በሐያት ሬጀንሲ ሆቴል ለሦስት ቀናት በተካሄደው በዚሀ ልዩ መርሐ-ግብር ላይ፣ ከ1200 በላይ ኢንቬስተሮች የተገኙ ሲሆን፣ በአዲስ አበባ አዲስ ስለሆነው የላጋሬ ዓለምአቀፍ የመኖሪያ እና የከተማ መዳረሻ በቂ ግንዛቤ በማግኘት፣ በኢንቨስትመንቱ ላይ ከፍተኛ ፍላጎት አሳይተዋል፡፡

በኢግል ሂልስ ኢትዮጵያ እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጥምረት የተገነባው ላጋሬ 1(አንድ)፣ 187 ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ እና ለመሀል ከተማ ኑሮ እጅግ የተመቹ ቅንጡ መኖሪያ ቤቶችን ያካተተ ሲሆን 360,000 ካሬ የሚያካልለው የላጋሬ ግንባታ፣ ለአዲስ አበባ እጅግ ውብና ቅንጡ አዲስ የከተማ ማዕከል ይፈጥራል፡፡ ከ4,000 በላይ መኖሪያ ቤቶችን የሚያርፉበት የላጋሬ ቅንጡ መንደር፣ ከቅንጡ የአኗኗር ዘይቤ በተጨማሪ፣ ለጎብኚዎች መስተንግዶነት፣ ለንግድ እና ለችርቻሮ፣ እንዲሁም ለእረፍትና ለመዝናኛ እጅግ የተመቸ መዳረሻ ይሆናል፡፡

ሚስተር ሎው ፒንግ፣ የኢግል ሂልስ ፕሮጀክት ዋና ስራ አስፈፃሚ፣ “የላጋሬ እጅግ የተለየ ግንባታ፣ በዓለም ዙርያ ለምናከናውናቸው አዳዲስ፣ አስደናቂና ቅንጡ የመኖርያ መዳረሻዎች ግንባታ ፕሮጀክቶቻችን እውን መሆን እውነተኛ ማሳያችን ነው፡፡ ላጋሬ፣ ተወዳዳሪ የማይገኝላቸውን የመኖሪያዎች እና የመዝናኛ አማራጮች ከማቅረቡም በተጨማሪ፣ የንግድ ልውውጥና የስራ እድሎችን በመፍጠር፣ ለማህበረሰቡ እና ለኢኮኖሚው ከፍተኛ አስዋፅዖ በማበርከት የአዲስ አበባ የልብ ምት እንደሚሆን ይታመናል፡፡ የላጋሬ 1(አንድ) ሽያጭ በይፋ መጀመር፣ ለራዕያችን መሳካት የመጀመሪያው ታላቅ እርምጃ ሲሆን፣ ይህንን ታላቅ ግንባታ፣ ለቤቱ የወደፊት ባለቤቶችና ነዋሪዎች ለማስተዋወቅ ዝግጅታችንን አጠናቀናል” ብለዋል፡፡

የባለ 21 ፎቁ፣ የረዥሙ ላጋሬ 1 (አንድ) ፣ ከባለ1 እስከ ባለ4 መኝታ አፓርታማዎች፣ የአዲስ አበባን ውበት ከከፍታ ለማየት የሚያስችሉ ሲሆን፣ በተፈጥሮ መብራት የተንቆጠቆጠ ሎቢው አስገራሚ ውበትን አጎናፅፈታል፡፡ ላጋሬ 1(አንድ) ለኗሪዎቹ የ24 ሰዓታት ሙሉ የደኅንነት ጥበቃ ከምቹ የመኪና ማቆሚያ ሥፍራ ጋር የተሟላለት አስተማማኝ የመኖሪያ ህንፃ ነው፡፡ ላጋሬ (ለገሃር) የፈረንሣይኛ ቃል ሲሆን፣ ለዘመናት የቀድሞው የአዲስ አበባ ባቡር ጣቢያ መጠሪያ በመሆን ያገለገለ ታሪካዊ ስም ነው፡፡ ለገሃር የአዲስ አበባ ማዕከል የነበረና ከተማዋን በማገናኘት ያገለገለ ቁልፍ ስፍራ ነው፡፡ አሁን ደግሞ የከተማዋ ዋና የመኖርያ እና የንግድ ማዕከል በመሆን ታሪካዊነቱን መልሶ ሊጎናፀፍ ነው፡፡ በባለ4 እና ባለ5 ኮኮብ ሆቴሎች፣ በችርቻሮ ንግድ ሱቆች፣ በመስሪያ ቤት እና የድርጅት ቢሮዎች፣ እንዲሁም በመኖሪያ ቤቶች የተከበበው ላጋሬ፣ ከቦሌ ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በ20 ደቂቃ ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ ለታሪካዊው የለገሃር ባቡር ጣቢያ እና ለአዲስ አበባ ዋና ዋና የንግድ ማዕከሎች እጅግ በጣም ቅርብ ነው፡፡

Call