La Gare Amharic Logo

በኢግል ሂልስ፣ በየጊዜው እያስፋፋናቸው ያሉ አዳዲስ የቢዝነስ አማራጮች፣ ማህበረሰባችን አዲሱን እና እያደገ የሚገኘውን የገበያ ዓለም በፍጥነት እንዲቀላቀሉ ዕድል የሚፈጥር ነው፡፡ በማህበረሰባችን ላይ ኢንቨስት በማድረግ የጋራ ግቦቻችንን መምታት እንደምንችል በሚገባ እናምናለን፡፡

የንግዱ ዓለም በፍጥነት እያደገ ይገኛል፡፡ እኛም ከፈጣኑ ለውጥ ጋር ለመራመድ ራዕይ ሰንቀን እና ግባችንን ከፍ አድርገን እየሰራን እንገኛለን፡፡

እያንዳንዱ ግንባታዎቻችን የመጪውን ዘመን ፈጣን ዕድገት ታሳቢ አድርገው የሚገነቡ ቢሆንም፣ ታሪካዊ ዳራችንን አለመልቀቅ የሚኖረውን ጠቀሜታ ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ በትናንት መነሻችን እና በነገው ራዕያችን መካከል ትልቅ ትስስር ለመፍጠር የታለሙ ናቸው፡፡

ማህበረሰባችን ለለውጥ ጥልቅ ፍላጎት ያለውና ነባራዊ ሁኔታዎችን ለመለወጥ በትጋት የሚሰራ ነው፡፡ ሁላችንም ከተለያዩ አካባቢዎች የተገኘን ሲሆን፣ የተለያዩ ልምዶቻችንን እና ዕውቀቶቻችንን በአንድ ላይ በማጣመር ሁሉንም ያማከለ እና ያሳተፈ ስኬታማ ስራ ለመስራት በአንድነት እንተጋለን፡፡

መደጋገፍ እና መተጋገዝ የተሞላበት የስራ ከባቢ መፍጠር ለእኛ እጅግ አስፈላጊና ጠቃሚ ነገር ነው! ማህበረሰባችን በታላላቅ ኢንቨስትመንቶቻችን፣ አዳዲስ አስተሳሰቦችን በመቀበል ችሎታችን እና አብሮ በመስራት ባህላችን አማካኝነት እምቅ ችሎታውን እና ብቃቱን በማውጣት ስኬታማ መሆን እንዲችል ይደረጋል፡፡

ማስታወቂያዎቻችንን ይመልከቱ

Call