La Gare Amharic Logo

በአዲስአበባ እንብርት ለገሃር በ 360,000 ካሬእስኵዌር ሜትር ላይ የሚገነባ የተቀናጀ የመኖሪያ፣የተለያዩ አገልግሎት መስጫና የመዝናኛ ስፍራዎች ልማት

በጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ የበላይ ጠባቂነት በአዲስ አበባ ለገሀር አከባቢ ስራዉን ለመጀመር ዝግጅቱን ያጠናቀቀዉ የዱባይ አቡዳቢው ኤግል ሒልስ (Eagle Hills) በአዲስአበባ ለገሃር የተቀናጀ የመኖሪያ፣አገልግሎት መስጫና የመዝናኛ ስፍራ ልማት ስራውን በይፋ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ በተገኙበት ህዳር 10/2011 አ.ም. ይጀምራል።

ይህ በ 360,000 እስኩዌር ሜትር መሬት ላይ የሚያርፈዉ የለገሐር የተቀናጀ የልማት ኘሮጀክት የአዲስአበባን መሐል ከተማ ወካይ ሆኖ በዉስጡ ከ 4000 በላይ መኖሪያ ቤቶች ፣የመዝናኛ ስፋራዎች፣ግዙፍ የንግድ ማእከላት ፣መጋቢና ዋና መንገዶች እና ሌሎች ዘመናዊ አገልግሎት መስጫ ስፍራዎች ይኖሩታል ።

ከቦሌ አለም አቀፍ አዉሮፕላን ማረፊያ በቅርብ ርቀት የሚሰራው ይህ ሁለገብ መንደር እንዲሁም ባለ አምስት ኮከብ ሆቴሎች ፣አረንጓዴ መዝናኛ ስፍራዎች ፣ምቹና ሰፋፊ የእግረኛ መንገዶች እና የመኪና ማቆሚያ ስፍራዎች በበቂ ሁኔታ በዉስጡ እንዳካተተም ማስተር ኘላኑ ያመለክታል።

ኘሮጀክቱ በኢትዮጵያ መንግስት እና በዱባዩ ኤግል ሒልስ ትብብር የሚሰራ ሲሆን ነዋሪዎች አሁን ባሉበት ቦታ መኖርያ ቤት ተገንብቶላቸዉ በዘላቂነት በሚያዉቁት ቀዬ እንዲኖሩም ይደረጋል።

ስለ ኘሮጀክቱ ፋይዳ ሲናገሩ የኤግል ሒልስ ሊቀ መንበረ ሞሀመድ አልባረ

“እንደ አንዷ የአፍሪካ እንቁዎች ኢትዮጵያ በባህል፣ ታሪክ እና የተፈጥሮ ዉበት የበለፀገች ነች ስለዚህ የእኛ ፍላጎት እንዲህ ዉብ ከሆኑት የሀገሪቱ ትሩፋቶች አንዱ የሆነውን በአዲስ አበባ የለገሃር አካባቢን አልምቶ አለም እንዲያውቀው እና ሰዎች ከተለያየ የአለም ክፍል ኢትዮጵያን መዳረሻቸው አድርገው ሁሉ ነገር የተሟላለት መንደር መኖር፣መዝናናት እና መገብየት እንዲችሉ ማድረግም ጭምር ነው።ከዚህ በተጨማሪም ይህ ኘሮጀክት ለአከባቢዉ ነዋሪዎችም ሆነ ለሌሎች የስራ እድል በመፍጠር የሀገሪቱን ኢኮኖሚ የበለጠ የማነቃቃት ሰፊ ሚና ይኖረዋል።”ብለው የዚህን ዘመናዊ ኘሮጀክት ሰፊ ጥቅም አስረድተዋል።

ለገሀር ከፈረንሳይኛ ቋንቋ የተወሰደ ሲሆን ትርጓሜዉም የባቡር ጣቢያ ማለት ነው ይኸውም የባቡር ጣቢያ በአዲስ አበባ ዋነኛ ጣቢያ በመሆን ለዘመናት አገልግሏል።

በአዉሮፓውያን የዘመን ቀመር በ1917 የተጠናቀቀው ጣብያዉ ለከተማዋ ብሎም ለኢትዮጵያ ዋነኛው የባቡር ትራንስፖርት ማእከልም ነበር።

አዲሱ የለገሀር ፕሮጀክትም በዉስጡ በጥልቅ የኪነ ህንፃ ጥበብ የሚሰሩ ለቢሮ አገልግሎት የሚዉሉ ህንፃዎች ሲኖሩት በቅርብ ርቀትም ባለ አራት እና አምስት ኮከብ ሆቴሎች ይገኛሉ።

የአቡዳቢዉ ኤግል ሒልስ ትልልቅ የተቀናጀ የመኖሪያ መንደሮች ግንባታ ድርጅት ሲሆን በተለያዩ ሀገሮች ብዙ ቁጥር ያላቸው መንደሮችን ገንብቷል።

ይህ ኩባንያ ተመሳሳይ መንደሮችን በአለም ዙሪያ ለመገንባት አቅዶ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል።
ኤግል ሒልስ በኢትዮጵያ
ኤግል ሒልስ በኢትዮጵያ የግል የመኖሪያ ቤቶች አልሚ ድርጅት ሲሆን ትልልቅ እሴት ያላቸው ግንባታዎች ላይ ተሳትፎ በማድረግ የሃገሪቱን የኢኮኖሚ እድገት በማፋጠን ረገድ የግሉን ድርሻ አበርክቶ ለማሕበራዊ እና ኢኮኖሚ እድገት አስተዋጽኦ ያበረክታል።

ይህ በዉበቱ እና ዘመናዊነቱ የላቀ እንደሚሆን የተነገረለት መንደር በዘርፉ ከፍተኛ እውቀት አና ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች የሚሰራ ከመሆኑም ባሻገር የአካባቢዉን አረንገጓዴነትና እና ለመኖሪያ ምቹነት ባገናዘበ መልኩ ይገነባል።

በ 360,000 እስኴር ሜትር ቦታ ላይ የሚያርፈው ፕሮጀክቱ የአነስተኛ ንግድ ስፍራዎችንም በዉስጡ የያዘ ሲሆን ዙሪያውም በመናፈሻ ፓርክ የተከለለ ነው ።
ፕሮጀክቱ ሰፋፊ የሰራ እድሎችን ከመፍጠሩም ባሻገር በሀገሪቱ ያሉትን የንግድ እንቅስቃሴዎች በእጅጉ ይደግፋል።

Call