La Gare Amharic Logo

ለገሀር ስካይ ጋርደን አንድ የመጀመሪያው በ ለገሃር የሚገነባው ህንጻ ሲሆን ባለ 1 ፣ ባለ 2 ፣ ባለ 3 እና ባለ 4 መኝታ የመኖሪያ
አፓርትመንቶችን ያካተተ ነው፡፡ ይህ ህንጻ ከ ለገሃር በስተ ሰሜን-ምሥራቅ አቅጣጫ ላይ የሚገኝ አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ እና የማህበረሰቡን የዕለት ተዕለት የጋራ አገልግሎቶችን በቀላሉ ለማግኘት እንዲያስችል ተደርጎ የተገነባ ነው፡፡

የህንፃው አቅራቢያ የንግድ ቦታዎች፣ የተለያዩ ቢሮዎች እና ባለ 4 ኮኮብ ሆቴል የሚገኙበት በመሆኑ፣ ለነዋሪዎች እና ለጎብኚዎች አመቺ እና
ሁለንተናዊ የህይወት ዘይቤን የሚፈጥር ነው፡፡

በራሪ ወረቀቱን
የክፍያ ዕቅድ ይመልከቱ

የወለሉን አቀማመጥ ይመልከቱ

አስደናቂ የሆነ ዲዛይን

የዘመናዊ ስነ ህንጻን ውበት እና ቀላልነት በማጣመር ስካይጋርደን አንድ አፓርትመንቶች በስራቸው መሪ በሆኑ አለም አቀፍ የ ስነ ህንጻ ባለሞያዎች ዲዛይን የተደረጉ እና በከፍተኛ ጥራት የተገነቡ ናቸው። የከተማውን ውብ ቦታዎች ለማሳየት ሰማይ ጠቀስ የሆነው ህንጻ ሁሉም ቤቶች ለመኖር የሚያስደስት ስሜት እንዲኖራቸው እና በአካቢው ላይ ምርጥ የሆኑ አገልግሎቶችን ለማግኘት በሚያስችል አቀማመጥ ላይ ናቸው።

ግሩም እይታ ያላቸው ቤቶች

የመኪና ማቆሚያዎችን ከታች ያካተተው ባለ 21 ፎቁ ህንፃ አስገራሚ እና ድንቅ በሆነ የመሬት አቀማመጥ ላይ የሚያርፍ ሲሆን የተዋቡ ፓርኮች ፣ የእግረኞችን መጓጓዣ መንገድ ፣ የባቡር መስመሩን፣ የአዲስ አበባን ዋና የንግድ ማዕከል እና ሩቅ ተሻግሮ አዲስ አበባን የከበቧትን የተራሮችን ውበት እያዩ መንፈስን የሚያድስ እና ቀልብን የሚስርቅ ገጽታ ይኖረዋል። የተፈጥሮ ብርሃንን ስሜት በሚያላብሱ ውብ መብራቶች የተንቆጠቆጠውና በህንፃው መግቢያ ላይ የሚገኘው የማረፊያ ሎቢ፣ በቤትዎ ውስጥ ያሉ ያህል ምቾት እንዲሰማዎት ያደርጋል። በህንጻው ለነዋሪዎች እና ለመኪኖቻቸው ደህንነቱን የጠበቀ የ24 ሰዓታት ንቁ የጥበቃ አገልግሎት ስለሚሰጥ ምቾትዎ በበቂ ሁኔታ ይጠበቃል፡፡

ሥፍራ ካርታ

whatsapp